ሁኔታውን ስናይ እየሆነ ያለውን
ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ሚመስለውን
ለምን ይኼ ሁሉ እግዚአብሔር ካለህ
ስትል ነፍስ ስትቃትት ኸረ ያምላክ ያለህ
አንተ ግን በዙፋንህ ተረጋግተህ
ተቀምጠሃል ሁሉንም አውቀህ
እግዚአብሔር ከጅማሬ እስከፍጻሜው
ባለቤት ነህ የታሪክ ጸሐፊው
ባንተ ማረፍ ነው መልካሙ ምርጫ
ሌላ እኮ የለም ከቶ ያለው ብልጫ
ኑሮ ሲወሳሰብ ሰዉ ግራ ገብቶት
ነገ አልታይ ብሎት ውሉ ሲጠፋበት
እግዚአብሔር እያለ ለምን ይኼ ሆነ
እያለ የሰው ልጅ እንቅልፍ ካይኑ ሸሸ
አንተ ግን በዙፋንህ ተረጋግተህ
ተቀምጠሃል ሁሉንም አውቀህ
እግዚአብሔር ከጅማሬ እስከፍጻሜው
ባለቤት ነህ የታሪክ ጸሐፊው
ባንተ ማረፍ ነው መልካሙ ምርጫ
ሌላ እኮ የለም ከቶ ያለው ብልጫ
ሁሉ እኮ በእጅህ ነው
አሳብህ ጥልቅ ነው
ላመኑብህ መታመኛ
እግዚአብሔር ነህ መዳኛ
ሁሉ እኮ በእጅህ ነው
አሳብህ ጥልቅ ነው
ላመኑብህ መታመኛ
እግዚአብሔር ነህ መዳኛ
ሁሉ እኮ በእጅህ ነው
አሳብህ ጥልቅ ነው
ላመኑብህ መታመኛ
እግዚአብሔር ነህ መዳኛ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist