ሁሉንም ፡ ትቼ ፡ እሮጣለሁ
ያለኝንም ፡ ሁሉ ፡ አጣዋለሁ
የሚጠቅመኝንም ፡ እተዋለሁ
ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር
አንድ ፡ ነገር ፡ እሻለሁ
እርሱንም ፡ አውቃለሁ
ሁሉም ፡ ቀርቶብኝ ፡ ቢገኝልኝ
የሱስ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ ፡ የናፈቀኝ
በእርሱ ፡ ተገኝቼ ፡ እርሱንም ፡ አግኝቼ
ሌላ ፡ መሻት ፡ የለኝ ፡ የምራበው
የሱስ ፡ ዕንቁዬ ፡ ነው
እርሱን ፡ ከማወቅ ፡ ጋር ፡ ምን ፡ ይወዳደራል
ሁሉን ፡ እርግፍ ፡ አድርጐ ፡ አስትቶ ፡ ያስኬዳል
ሽልማቴ ፡ ሌላ ፡ መች ፡ ለእኔ ፡ ሆነልኝ
እርሱ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ
ሽልማቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ሽልማቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ሆነህ ፡ ተገኝተሃል ፡ በእኔ ፡ ዘንድ ፡ አንደኛ
ሁሉንም ፡ አስናቀኝ ፡ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡
የከበረ ፡ የገነነ ፡ እኔ ፡ እምሻው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist