Kishore Kumar Hits

Ebba Daniel - Marken lyrics

Artist: Ebba Daniel

album: Yehagere Lij


ልክ እንደፈራጅ ከልቡ መዝገብ በአፉ መርገም በደል ቆጣሪ
እንዲያ ሳትሆን ጨካኝ አባት ፍቅርን ከለላን ነፍጎ አባራሪ
እግዚአብሔር ሆይ ዘላለማዊው ፍቅርህ ብዙ ነው አያልቅ ተነግሮ
የምህረትህ የቃልህ እውነት ቤትህ አስገባን እኛንም ምሮ
ማርከን ማርከን ጌታ ሆይ ማርከን
ማርከን ማርከን አንተ ግን
የምንራመድ በጥፋት መንገድ
የምንነዳ በኀጢአት ሞገድ
ያዳነንን ፀጋህን ረስተን
የውድቀት ፍሬ ያኔ አነቀን
ከግብፅ ህይወት ዛሬም ስንፈልግ ጠፍተን በምኞት ስንሄድ የኋሊት
ተስፋ እያለን ግን ተስኖን ኋላውን ትተን ማየት ወደፊት
ማርከን ማርከን ጌታ ሆይ ማርከን
ማርከን ማርከን አንተ ግን
ሳይረፍድ ሳይዘገይ ከውድቀታችን ቀደምክ
ስንቱን በደል መርገም ከእኛ አስወገድክ
በቤትህ ቆመናል አንተን ተመርኩዘን
ትላንትን አለፍን እጆችህን ይዘን
ዛሬም እንድንኖር ነገም እንዳንጠፋ
በአንተ ምህረት ላይ አለን ሙሉ ተስፋ
ማርከን ማርከን ጌታ ሆይ ማርከን
ማርከን ማርከን አንተ ግን
ማርከን ማርከን ጌታ ሆይ ማርከን
ማርከን ማርከን አንተ ግን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists