Ebba Daniel - Endeweta Kere lyrics
Artist:
Ebba Daniel
album: Yehagere Lij
በታናሽነቱ ህልም አየሁ ስላለ
በገዛ ወንድሞቹ ከጉድጓድ ተጣለ
ወደ ወህኒ ቢወርድ ቢያልፍም በእስራት
መጣል መገፋቱ ሊሆነው ለምክኒያት
ተጥሎ በግዞት ከነህልሙ ታስሮ
መፍትሄ መልስ ሆኖ ለሌሎች ቋጠሮ
ለበርካታ ወራት ሲኖር ከነህመሙ
ህልምን እየፈታ ተፈታለት ህልሙ
የእግዚአብሔር ሀሳብ ልቡ ያረፈበት
መውጣቱ አይቀርም ክብር ወዳለበት
የከፍታው ዘመን እንዲህ እየጨመረ
ላይወርድ ከማማው ላይ እንደወጣ ቀረ
አሀሀሀ በክብር ደረሰ
ኦሆሆ ከፍታውን ያዘ
አሀሀ አምላኩ ካየለት
ኦሆሆ በክብር ደረሰ
ለሀሠት የቀና ህሊናው ታውሮ
ወንጌሉን ሲገፋ ሲያሳድድ ኖሮ
አገልጋዩ ሆነ በምህረት ቆሞ
በምድሪቱ ዞረ ወንጌል ተሸክሞ
ላመነበት እውነት ሰውቶ ህይወቱን
ከባርነት ዐለም አፈለሰ ስንቱን
በዘመኑ ሮጦ የፅድቅን እሩጫ
በአምላኩ ቀኝም ኖረው መቀመጫ
የእግዚአብሔር ሀሳብ ልቡ ያረፈበት
መውጣቱ አይቀርም ክብር ወዳለበት
የከፍታው ዘመን እንዲህ እየጨመረ
ላይወርድ ከማማው ላይ እንደወጣ ቀረ
አሀሀሀ በክብር ደረሰ
ኦሆሆ ከፍታውን ያዘ
አሀሀ አምላኩ ካየለት
ኦሆሆ በክብር ደረሰ
በአምላኩ መንገድ በፅድቅ የተጓዘ
በአካሄድ በኑሮው እውነትን የያዘ
በስኬት ሠገነት ሃይሉን አያደሰ
እንደወጣ ከላይ ካለመው ደረሰ
የእግዚአብሔር ሀሳብ ልቡ ያረፈበት
መውጣቱ አይቀርም ክብር ወዳለበት
የከፍታው ዘመን እንዲህ እየጨመረ
ላይወርድ ከማማው ላይ እንደወጣ ቀረ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist