Kishore Kumar Hits

Mesay Tefera - Degeye lyrics

Artist: Mesay Tefera

album: Degeye


አንዳንድ ጊዜ ግርም ይለኛል
ውድ ያሉት ሁሉ ይረክስብኛል
አሄሄ
አሉና ጎኔ ብዙ ያላቸው
ግን አንድ ነገር የጎደላቸው
አሄሄ
አንቺዬ ምንድነው ህይወት
ከሌለው ሰው እንዳንቺ አይነት
መውደድን ቃል አልፎ
አየሁት እኔ ባንቺ ምግባር
በሰው ላይ በሰው ላይ
በሰው ላይ ምን ቢያምር
ድንግርግርግር ይላል ከበሮና ፍቅር
ላንቺ ግን ላንቺ ግን
ላንቺ ለደጊቱ
ቀላል ሆኖልሻል የተናገርሽውን ሆኖ መገኘቱ
እህህ
እህህ
እህህ
እህህ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደጊቱ
ያላዋቂው መላ ያለባለቤቱ
እፍ ቢሉትማ አይነድም እሳቱ
የኔም ልብ ዜማው
ያላንቺ አይጥም ስልቱ
ሲያረግቡት እሳት
ሲለኩሱት መንደድ
ሲያረግቡት እሳት
ሲለኩሱት መንደድ
እንዲህ ያደርጋል ወይ
የሸጋ ልጅ መውደድ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ
ይጨምርላታል
የልቧን እያየ
እህህ
እህህ
እህህ
እህህ
መረረር ያለ ቃል አይቀናት
ሸለክላካው መንገድ አይጥማት
ነፃ ነች የእውነት ተክና
አያስራት የንፍገት ካቴና
የምሽት የቀኑም ፈረቃ
ፀሐይም ኮከብም ጨረቃ
ሰው ሆነው ከታዩ በምድር
እሷ ነች ያላንዳች ጥርጥር
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደጊቱ
እንኳን ተጎዝጉዞ ቄጠማው ከደጇ
እንኳን ተጎዝጉዞ ቄጠማው ከደጇ
ደረቁ ለምለም ነው ስትይዘው በእጇ
መረቋት መረቋት እንደምን እናቷ
መረቋት መረቋት እንደምን አባቷ
ፀዳል ልብ የሰጣት ልክ እንደውበቷ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ
ይጨምርላታል
የልቧን እያየ
ደግዬ ደግዬ
ደግዬ ደግዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists