ሰመመን ውስጥ ሆና ነፍስ ትቃዣለች
ላፍታ እንኳ አተኛም ትባንናለች
ያዝኩ ስትለው እድል ያመልጣል
ደረስኩ ስትለው ደግሞ ይሸሻታል
መጨረሻው ቢሆንስ ህይወት ተገባዶ
ጊዜ መቁጠር ቢያቆም ስራውን ጨርሶ
እድሜ በዝቶ ነበር ቁጥር ተከማችቶ
ግን ምን ይሰራል እጅ ባዶ ቀርቶ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
ነፀብራቁን ብታይ መስታወት ፊት ሆና
አይኖቿን ከደነችው ሀፍረት ተከናንባ
ልታሳይ ብትሞክር ስራዋን በእምባ
ሽንፈት አድቋታል ተጎሳቁሏል ፊቷ
መጨረሻው ቢሆንስ ህይወት ተገባዶ
ጊዜ መቁጠር ቢያቆም ስራውን ጨርሶ
እድሜ በዝቶ ነበር ቁጥር ተከማችቶ
ግን ምን ይሰራል እጅ ባዶ ቀርቶ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
ጅቡ ቢመለስ ውሻው ሞተ
ጌታው ቢወጣ ጩኸት ሰምቶ
ጅቡም የለም ውሻው ሞቶ
ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
ጅቡ ቢመለስ ውሻው ሞተ
ጌታው ቢወጣ ጩኸት ሰምቶ
ጅቡም የለም ውሻው ሞቶ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
ከራስ ጋር ፍልሚያ
ከራስ ጋር ክርክር
ከራስ ጋር ሽኩቻ
ከራስ ጋር ግብግብ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist