አበባዬ ነይ ናርዶስ ገላ ይስባል ሽታሽ
ያውደኝ መዓዛሽ
እስኪ ብቅ ውጪ ፈክተሽ የኔ አማላይ
ደስታዬ አንቺን ሳይ
ብስም አልጠግብሽ ብቀስም አልረካ
እምቡጥ ከንፈርሽን ሁሉሽን ብነካ
ብስም አልጠግብሽ ብቀስም አልረካ
እምቡጥ ከንፈርሽን ሁሉሽን ብነካ
መዓዛሽ የገነት ቃልሽ የነብስ ምግብ
ነሽ ያይን ማረፊያ
ከት ብለሽ ስቀሽ እንኳን ጥርስሽ ታይቶ
ያምርብሻል ኩርፊያ
ደግነት ያሳያል ይራራል ምግባርሽ
ውበትሽ ሙሉ ነው
አበባዬ ባንቺ
እኮራለሁ እኔ እመፃደቃለሁ
ፍኪልኝ አበባዬ
ታይልኝ አብበሽ
በእናት በአባት ምርቃት
ከሰው መሀል ጎልተሽ
ብወድሽ ብወድ አልጥግብሽ
በፍቅር አንቺን አልበልጥሽ
ብወድሽ ብወድ አልጥግብሽ
አልጠግብሽ
አበባዬ አንቺ አበባዬ
ናርዶስ ሽቶ ውቧ አበባዬ
አበባዬ የማር እናቱ
ፋኖስ ኩራዝ መብራት ለቤት
አበባዬ ውቧ አበባዬ
ከንፈርሽን አልጠግብሽ ስሜ
አበባዬ ስሱ ገላሽን
ነድፈዋለሁ የሚነካሽን
አበባዬ የወይን አበባ
በእቅፍ ይዤ አጅቤሽ ልግባ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
አፍሽ ልብሽ ገራም ክፉ ወጥቶሽ አያውቅ
ታፋጭ ትርንጎ ጣዕም
የእሸት ዘለላ በእጅ አሽቶ እፍ ብሎ
ከአዝመራ እንደመቃም
ሐምራዊ ሐር መስሎ በጌጥ ተጎንጉኖ
ተሾርቧል ፀጉርሽ
ውብ ናቸው አይኖችን
ከወይን ከሮማን ይጥማል ከንፈርሽ
ፍኪልኝ አበባዬ
ታይልኝ አብበሽ
በእናት በአባት ምርቃት
ከሰው መሀል ጎልተሽ
ብወድሽ ብወድ አልጥግብሽ
በፍቅር አንቺን አልበልጥሽ
ብወድሽ ብወድ አልጥግብሽ
አልጠግብሽ
አበባዬ አንቺ አበባዬ
ናርዶስ ሽቶ ውቧ አበባዬ
አበባዬ የማር እናቱ
ፋኖስ ኩራዝ መብራት ለቤት
አበባዬ ውቧ አበባዬ
ከንፈርሽን አልጠግብሽ ስሜ
አበባዬ ስሱ ገላሽን
ነድፈዋለሁ የሚነካሽን
አበባዬ የወይን አበባ
በእቅፍ ይዤ አጅቤሽ ልግባ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
አጅቤሽ ልግባ አጅቤሽ ልግባ
የኔ አበባ የኔ አበባ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
ኦሆሆይይ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist