ፍቅረኛ ነበርን እኔና አለሚቱ
ንዋይ በለጠባት ማረካት ውበቱ
ልቤን ሰበረችው እንክትክት አድርጋ
መሽቶ ሚቀር መስሏት ለኔም የማይነጋ
ክድሀለችና በግልፅ ባደባባይ
ነግርሀለችና እንደሆነች አባይ
እንግዲህ እወቅበት በጊዜ ተሰብሰብ
በዚህ አያበቃም የአለሚቱ ሰበብ
አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
ይመስገን ገንዘብ አመል ገላጩ
ጓደኝነትሽ ቀረ በእንጭጩ
እኔም ሄዳለው ድምፄን አጉልቼ
ፍቅርን ይዤ ንዋይን ትቼ
አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
ብርቅ ያረኩት እኔ ባንቺ መከዳቱ
አንቺ ምን ታደርጊ ካልገባኝ እውነቱ
በማር ቢለወስ ቃል ቅቤ ቢያቀልጥ ምላስ
ምን ያረጋል ብለሽ ሁለት ካጣ አንድ ራስ
በማር ቢለወስ ቃል ቅቤ ቢያቀልጥ ምላስ
ምን ያረጋል ብለሽ ሁለት ካጣ አንድ ራስ
ለአንገት የሚቀል የለም እንደራስ
ችዬ ኖራለው አልሻም ትራስ
ስንደልቅ ነበር አብረን ከበሮ
ኪሴ ተቀዶ ባላውቅሽ ኖሮ
አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
ሳላውቅ አመልሽን ሆንኩኝ መዛበቻ
ውልሽ የአጭር ጊዜ ከሞላለት ብቻ
አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
ፍቺኝ አለም (ፍቺ ፍቺ)
በቃኝ አለም (በቃኝ በቃኝ)
ይቅር አለም (ይቅር ይቅር)
ዞርበይ አለም (ዞርበይ ዞርበይ)
(ፍቺ ፍቺ)
(በቃኝ በቃኝ)
(ይቅር ... ዞርበይ ዞርበይ)
አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist