Rahel Getu - Hahu lyrics
Artist:
Rahel Getu
album: Etemete
ሀሁ ለሉ ብዬ በመውደድ ስማር
እውቀቴን ገነባሁ ያንደበትህ ማማር
ሁል ጊዜህ አፍህ ላይ ልጣለው ጆሮዬን
ባንተ አለምን ሳውቃት ወደድኩት ኑሮዬን
ይሂው በአነጋገር በኑሮ በስዬ በስዬ
ታየሁ በሰዎች ፊት አስተዋይ መስዬ መስዬ
ዘንድሮ ተደነኩ በማፈልቀው ሃሳብ አይ ሃሳብ
ቁም ነገር አግኝቼ በአንደበትህ ስሳብ አይ ስሳብ
ሊቄ ነህ መምሬ ለፍቅር ጅማሬ
ፍቅርን ለማወቄ የኔታ ጠቢቤ
♪
ልጅ ናት ይሉኝ ነበር ከበፊት የሚያቁኝ
ዛሬ አዋቂ አድርገው በሰፊው ጠየቁኝ
ለሁሉም ስመልስ መች አፈርኩብህ
ከልቤ ነው እና የተማርኩብህ
ገልጸህ ያሳያኸኝ ሁሉን እንድረዳ
ፊደሌ ሆነሃል የህይወቴ አቦጊዳ
በሃሳብ አሻራ ላይ እያሰነበትከኝ
ከቅኔው ሊቃወውንት ተርታ የከተክኝ
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ
♪
ፊደሌ ብልህስ መች አንተን ይገልፃል
እንደ ህይወቴ ድርሳን ልቤ ያነብሃል
ሀ ግዕዝ ሁ ካዪብ እያልኩኝ በስምህ
እንደ ዳዊቴ ነው የምደጋግምህ
ቀርቦ ለሚያደምጠው ንግግርህ ሲያምር
ሂዎትን ያቃናል ያንተ ቃል ሲያስተምር
ነብስን ትገራለህ ባደለህ አንደበት
አሁንም አሁንም ደጋግመህ አውራበት
እሮጬበታለው የልጅን መንገድ
ካሰቡት ያደርሳል ያወቀን መውደድ
በጥበብህ ስበህ ከልብህ ስትከተኝ
ጥሩ ሄጃለው ወይ ስትመለከተኝ?
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ
ሀሁ በእድሜ ከፍ እስክል ሀሁ እውቀት እንዲኖረኝ
ሀሁ እናቴ ነበረች ሀሁ ሁሉን የምትመክረኝ
ሀሁ የሂዎትን ጽናት ሀሁ ከእሷ ተምሬአለሁ
ሀሁ ባንተም ስለ ፍቅር ሀሁ ማወቅ ጀምሬአለሁ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist