Kishore Kumar Hits

Rahel Getu - Beketemaw lyrics

Artist: Rahel Getu

album: Etemete


ቢታይ ከተማው ከተማው
ቢታይ ከተማው ቢታይ ከተማው
ቢቃኝ መዲናው መዲናው ቢቃኝ መዲናው
የታለ ግርማ ለካስ ውበቱ አንተነህ ድምቀቱ
ከሌለህ ጭር ይላል ካለህ ሁሉም ያምራል

የፀሐይ ከምፈል መሬቱን ስቦ ሲነጋ ለሊቱ
የለህም እንደው ዓይኖቼ ናፍቀው ሲንከራተቱ
የደበዘዘው ቀኑ የሚፈካ
የሚወዱት ሰው ሲኖር ነው ለካ
የትም ቤቴ ነው የትም ሃገሬ
ካንተጋር ሁሉ ሰላም ነው ፍቅሬ
ዘወርዋራው መንገድ ዘወርዋራው
ሳይገድበኝ ካለህበት ስፍራ
መጥቻለሁ ፍቅርን እንደተጠማሁ
ላይህ በከተማው
(በከተማው) በከተማው
(በደጅህ) አንዴ ልይህ
(በከተማው) በከተማው
(በደጅህ) ብቅ በል ልይህ

ቢታይ ከተማው ከተማው
ቢታይ ከተማው ቢታይ ከተማው
ቢቃኝ መዲናው መዲናው ቢቃኝ መዲናው
የታለ ግርማ ለካስ ውበቱ አንተነህ ድምቀቱ
ከሌለህ ጭር ይላል ካለህ ሁሉም ያምራል

የአየሩ ፀባይ ደመና ሆኖ ሲያልፍ ንፋስ
እጅህን በእጄ አቆላልፌው ሙቀት ልዋዝ
ደም ሲያተኩስ የጀምበር ገላ
ዛፍ ቁመትህን ታደርገው ጥላ
የልምዴን መርጠው ሁሉንም ጥዬ
አንተን ካገኘሁ ምን አጣሁ ብዬ
ዘወርዋራው መንገድ ዘወርዋራው
ሳይገድበኝ ካለህበት ስፍራ
መጥቻለሁ ፍቅርን እንደተጠማሁ
ላይህ በከተማው
(በከተማው) በከተማው
(በደጅህ) አንዴ ልይህ
(በከተማው) በከተማው
(በደጅህ) ብቅ በል ልይህ
(በከተማው) በከተማው
(በደጅህ) አንዴ ልይህ
(በከተማው) በከተማው
(በደጅህ) ብቅ በል ልይህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists