Rahel Getu - Tirefi lyrics
Artist:
Rahel Getu
album: Etemete
ጥድፍ ጥድፍ እያልኩ በሚገርም እሩጫ ሳላውቅ በልጅነት
በዚች አጭር እድሜ ያየሁትን ዳገት ሜዳ እና ቁልቁለት
ቆም ብዬ ዛሬ ሳየው ይገርመኝል ትረፊ ባይለኝ
ምን ይወጣኝ ነበር ፈጣሪ ሊረዳኝ አንተን ባይሰጥኝ
ትረፊ ቢላት ነው ትረፊ ሲላት ለምስኪኗ ልቤ አንተን ያደላት
አብቢ ቢላት ነው ላስውብሽ ሲላት ለተዘጋው ቤቴ አንተን የሰጣት
♪
አምላክ እራሱ ነው ታምሩን እንዳውጅ ቆሜ የሱን ስራ
በጥላው ሸሽጎ እጣዬን የጻፈው ፍቅሬን ካንተ ጋራ
እንደ እኔማ ቢሆን እንደ ፍላጎቴ ሁሉን ለማየት
ይዞኝ ይሄድ ነበር እንደ ደራሽ ዉሃ የራሴው ፍጥነት
ትረፊ ቢላት ነው ትረፊ ሲላት ለምስኪኗ ልቤ አንተን ያደላት
አብቢ ቢላት ነው ላስውብሽ ሲላት ለተዘጋው ቤቴ አንተን የሰጣት
♪
ጥድፍ ጥድፍ እያልኩ በሚገርም እሩጫ ሳላውቅ በልጅነት
በዚች አጭር እድሜ ያየሁትን ዳገት ሜዳ እና ቁልቁለት
ቆም ብዬ ዛሬ ሳየው ይገርመኝል ትረፊ ባይለኝ
ምን ይወጣኝ ነበር ፈጣሪ ሊረዳኝ አንተን ባይሰጥኝ
ትረፊ ቢላት ነው ትረፊ ሲላት ለምስኪኗ ልቤ አንተን ያደላት
አብቢ ቢላት ነው ላስውብሽ ሲላት ለተዘጋው ቤቴ አንተን የሰጣት
እሱ አስደንቆኝ ነው በዘዎትር ጸሎቴ አምላኬን ማንሳቴ
እኔ ባልኩት ሳይሆን ባቀደልኝ መንገድ ኑሮዬን መግፋቴ
ለካስ እሱ ነበር ጉዞና መነሻው በክብር ሲያዩት
ሰው ስንቁን ጨርሶ ከእግሩ ስር እንዲወድቅ ለሌላ ችሎት
ትረፊ ቢላት ነው ትረፊ ሲላት ለምስኪኗ ልቤ አንተን ያደላት
አብቢ ቢላት ነው ላስውብሽ ሲላት ለተዘጋው ቤቴ አንተን የሰጣት
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist