Kishore Kumar Hits

Rahel Getu - Neber lyrics

Artist: Rahel Getu

album: Etemete


ነበር ነበር
ነበር ነበር

አታሎኝ የቅርቤ ሆነ ሩቅ መስሎኝ
ታዘብኩት ነበር ሲሆን አለ ያልኩት
አታሎኝ የቅርቤ ሆነ ሩቅ መስሎኝ
ታዘብኩት ነበር ሲሆን አለ ያልኩት

ለካ እንዲ ቅርብ ነው ነበር
የወጠኑት ያሰቡት ሲቀር
እየለመነ አንሰማም ብንል ከመስመር ወቶ
ነበር ተባለ ፍቅራችን ሞቶ
ነበር ተባለ ፍቅራችን ሞቶ

የት ሄደን ነበር ምንስ ጋረደን
እያልኩ እራሴን ስጠይቅ ካለፈ
ምንም አልቻለም ባስብ ሊገባኝ
ፍቅራችን ድንገት እጃችን ላይ እንዴት እንዳረፈ
ለምን አቃተን ማሰብ መገንዘብ
ምን ሆነን ታወርን እላለው በእውነቱ
እንዴት የዛኔ አልታይ አለን አሉ መባሉ እንደሚሻል ነበር ከማለቱ
ሁለት ጌቶች በአንድ ቤት ሆነ ነገሩ ሆነና
ይሄው ቀረን በፉክክር ነበሩ ሆንን እና
ላይመለስ ባይፈይድም ዛሬ መቆጨቱ
ያሳዝናል ያ ፍቅራችን በነበር መቅረቱ

ለካ እንዲ ቅርብ ነው ነበር
የወጠኑት ያሰቡት ሲቀር
እየለመነ አንሰማም ብንል ከመስመር ወቶ
ነበር ተባለ ፍቅራችን ሞቶ
ነበር ተባለ ፍቅራችን ሞቶ

ያ ሁሉ እቅድ ያሁሉ ምኞት እንዲ መቅረቱ ሄደን በየግል
አንተ እንዳልከው ብሎ ማለፍ ነው አይችልም እና ሰው ሊገጥም ከአምላክ ጋር ትግል
እኔ ብሞክር ያቃተኝ ነገር አልመጣ ያለኝ የፀፀት እሳቴ
ላገኘኝ ሁሉ እስኪሰለቸው አለኸኝ ለሰው እንዳላልኩ ነበርክ ማለቴ
ያኔ እንደዛ እንዳልነበረ አለ የተባለ
እንዴት ባንዴ ያፍቅራችን ነበረ ተባለ
እንዲ ባንዴ ከተጋቡ ቀን እና ፅልመቴ
አቤት ህመም አለው እያልኩ ነበርኩኝ ማለቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists