Kishore Kumar Hits

Rahel Getu - Tilobign lyrics

Artist: Rahel Getu

album: Tilobign


እህህህህህህ
ስሌት የማይፈታው መልስ የማይመልሰው
የሌለው ማርከሻ
ሰሙ ቢሆንብኝ
የቃላት የቅኝት የከንፈር ማሟሻ
የዜማ ዜማ የሃሳቤ መነሻ መድረሻ
ዓለሜ ነው ለእኔ
እሱማ ለእኔ
እሱማ ለእኔ
እሱማ የትንፋሼ ዜማ
አውቀው ቢያሳውቁኝ
ምን አለ ለእኔ
ምን አለ ፍቅሬ የቱጋ እንዳለ
ዓለሜ ነው ለእኔ
እሱማ ለእኔ
እሱማ ለእኔ
እሱማ የትንፋሼ ዜማ
አውቀው ቢያሳውቁኝ
ምን አለ ለእኔ
ምን አለ ፍቅሬ የቱጋ እንዳለ
አሄሄሄ ይሆን ወይ አንዳንዴ
የኮከብ መገጣጠም
አሄሄሄ መልስም ጥያቄ ነው
የስሜቶች መርዘም
አሄሄሄ ይህ ወይናደጋ
አይሞቀው አይበርደው
አሄሄሄ እንደ ሐይቅ ሰንበሌጥ
ልቤን እኮ አራደው
ጥሎብኝ እሱን ወድጃለሁ
ካልመጣስ እንዴት እሆናለሁ
ነግሦብኝ በኔ ከከረመ
ለምን ወደድሺው እንዳትሉኝ
ደርሶበት ያየ እስኪ ይፍረደኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ቀልቤ ከተናጋ
ቀልቤ ከተናጋ የእሱን ስም ጠርታችሁ
ሀሰት ነው መኖሬ
ውሸት ነው መኖሬ እኔው ልንገራችሁ
የፍቅር ልክ ሆኖ
የመውደድ ጥግ ሆኖ በኔው ከራርሞብኝ
እንዴት ወደደችው
እንደምን ወደድሽው ባካችሁ አትበሉኝ
ጥሎብኝ እሱን ወድጃለሁ
ካልመጣስ እንዴት እሆናለሁ
ነግሶብኝ በኔ ከከረመ
ለምን ወደድሺው እንዳትሉኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
አሄሄሄ መልሱን ብትጠይቁም
ምኑን ነው የምላችሁ
አሄሄሄ የወደድኩት እሱን
ብዬ ልንገራችሁ
አሄሄሄ የቀስተደመና
ሕብር የበዛበት
አሄሄሄ እንዲያ የሚሆንባችሁ
እንዲህ ነው ስትሉት
ምኑን ነው
ዓይኑን ነው
ምኑን ነው
ጥርሱን ነው
አልልም አንዴ ወድጃለሁ
ካልመጣስ እንዴት እሆናለሁ
ነግሦብኝ በኔ ከከረመ
ለምን ወደድሺው እንዳትሉኝ
ደርሶበት ያየ እስኪ ይፍረደኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ
ጥሎብኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists