Kishore Kumar Hits

Jano Band - Shegiye lyrics

Artist: Jano Band

album: Lerasih New


ሸግዬ ቆንጅዬ
ብትሆን ምርጫዬ
ሰርቄ ባይኖቼ
አየሁህ ሰስቼ
ሃሳቤን ሲቀማኝ ፈገግታህ ከወዲያ
እንዴት ይሁን ታዲያ
ከንፈሬን ሰንጥቆት የሸጋ ልጅ ድርቅ
ምን ያስጠይቀኛል ለጥሜ ብሰርቅ
ከቆንጅናህ ጅረት ሞልቶ ከሚፈሰው
ጥፋት ይሆናል ወይ ጨልፌ ብቀምሰው
ምንጭ ዳር ጠውልጎ እንዴት ይሞታል ሰው
አሄሄሄሄ
አሄ ገባህ ካይኔ
እህ ምን ላርግ እኔ
አሄ ሌብነቴ
እህ በማጣቴ
አሄ ገባህ ካይኔ
እህ ምን ላርግ እኔ
አሄ ሌብነቴ
እህ በማጣቴ
ሸግዬ ቆንጅዬ
ብትሆን ምርጫዬ
ሰርቄ ባይኖቼ
አየሁህ ሰስቼ
ሃሳቤን ሲቀማኝ ፈገግታህ ከወዲያ
እንዴት ይሁን ታዲያ
ውበት ቀዳሽ ብለው አላዝንም ቢከሱኝ
ፈሰህ መምጣትህን ሲያውቁ ለሚክሱኝ
በመልክህ ወድቄ ምን እፎክራለው
ወይንጠጅን መቅመስ መች እሞክራለው
አልኮል እንዳበዛ ሳይህ እሰክራለው
አሄሄሄሄ
አሄ ገባህ ካይኔ
እህ ምን ላርግ እኔ
አሄ ሌብነቴ
እህ በማጣቴ
አሄ ገባህ ካይኔ
እህ ምን ላርግ እኔ
አሄ ሌብነቴ
እህ በማጣቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists