Kishore Kumar Hits

Jano Band - Engida lyrics

Artist: Jano Band

album: Lerasih New


እንግዳ ልጅ ነይ ነይ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ, እንግዳ
ልቤ አስቦሻል ነይ ነይ
አይኔ ናፍቆሻል ነይ ነይ, እንግዳ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ, እንግዳ
ልቤ አስቦሻል ነይ ነይ
አይኔ ናፍቆሻል ነይ ነይ, እንግዳ
ስወጣ በብርታት ላበጃጀው መስኩን
ለከርሞ አዝመራ, ለከርሞ አዝመራ
ትዝታሽ በርትቶ ብክን ያረገኛል
ናፍቆት እየዘራ, ናፍቆት እየዘራ, ናፍቆት እየዘራ
ፍቅርን አድሎኛል ብዬ ተኩራርቼ
ደረቴን ስነፋ, ደረቴን ስነፋ
ጉድ ይላል ሀገሬው ደሞ ቀርተሽብኝ
አንገቴን ስደፋ, አንገቴን ስደፋ, አንገቴን ስደፋ
እንኳን ተላምዶና, አሃ, በፍቅር ተሳስሮ
ይገናኝ የለም ወይ, አሃ, የተጣላ ዞሮ
መንገድ መንገድ ማየት, አሃ, ባሰ ጥበቃዬ
ናፍቆትሽ ሳይገለኝ, እእእ, ነይ ነይ እንግዳዬ
እንግዳዬ, ካንቺ ነውና ጉዳዬ
እንግዳዬ, ነይ ነይልኝ አበባዬ
እንግዳዬ, ውድ የፍቅር ስጦታዬ
እንግዳዬ, ነይ ነይልኝ አበባዬ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ, እንግዳ
ልቤ አስቦሻል ነይ ነይ
አይኔ ናፍቆሻል ነይ ነይ, እንግዳ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ
እንግዳ ልጅ ነይ ነይ, እንግዳ
ልቤ አስቦሻል ነይ ነይ
አይኔ ናፍቆሻል ነይ ነይ, እንግዳ
ሰማይ ሲያስገመግም ሞፈሩን በርትቶ
አልይዝ ሲለኝ ክንዴ, አልይዝ ሲለኝ ክንዴ
ምን ያልተባልኩልሽ አለና ባገሩ
አንቺን በመውደዴ, አንቺን በመውደዴ, አንቺን በመውደዴ
ተዉኝ አትጠይቁኝ መድሀኒት አልሻም
ሀኪም አትል ነብሴ, ሀኪም አትል ነብሴ
ሳያት ታያላችሁ ክንዴም ሲበረታ
ስታረቅ ከራሴ, ስታረቅ ከራሴ, ስታረቅ ከራሴ
እንኳን ተላምዶና, አሃ, በፍቅር ተሳስሮ
ይገናኝ የለም ወይ, አሃ, የተጣላ ዞሮ
መንገድ መንገድ ማየት, አሃ, ሳይብስ ጥበቃዬ
ናፍቆትሽ ሳይገለኝ, እእእ, ነይ ነይ እንግዳዬ
እንግዳዬ, ካንቺ ነውና ጉዳዬ
እንግዳዬ, ነይ ነይልኝ አበባዬ
እንግዳዬ, በናፍቆትሽ ተዳክሜ
እንግዳዬ, ሳልሞት ድረሽ ውብ አለሜ
ኦኦኦ ኦኦ
ኦኦኦ
ኦኦኦ ኦኦ
አሃሃሃሃ አአአአ
አሃሃሃሃ አአአአአ አምም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists