Kishore Kumar Hits

Jano Band - Gudie Fela lyrics

Artist: Jano Band

album: Lerasih New


ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ካምናው ተምሬ እፎይ ሳልል ታምቼ ባገር
እዩኝ በፍቅር ይኸው ደግሞ ዛሬም ስሸበር
የምን መውደድ ስል ከርሜ ስመከር
ምን ይባላል አሁን ዞሬ ስነከር
አምሮትን አውጥቶ ሽሽግ የሚደረግ
ሸበላ ባይ የወይን ሀረግ
በጭንቅ ያሣለፍኩት ታሪክ ተረሳና
ክንፍ አልኩኝ እንደገና
ፍርጃ ነው እንጂ መች አድሎኝ
ገና በሩቁ ሄዷል ገሎኝ
ቀድሞ እየጣለ ስንቱን ገላ
ተራምዶኝ ሄደ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ካምናው ተምሬ እፎይ ሳልል ታምቼ ባገር
እዩኝ በፍቅር ይኸው ዛሬም ስሸበር
የምን መውደድ ስል ከርሜ ስመከር
ምን ይባላል አሁን ዞሬ ስነከር
ሎሚ ጣይ ባገሩ ሌላም እንደሌለ
አሻፈረኝ
እምቢ እያለ
ስርስሩን ሲል ልቤ እኔም ሀይ አላልኩት
እንጃ ብቻ ተከተልኩት
ፍርጃ ነው እንጂ መች አድሎኝ
ገና በሩቁ ሄዷል ገሎኝ
ቀድሞ እየጣለ ስንቱን ገላ
ተራምዶኝ ሄደ ጉዴ ፈላ
ፍርጃ ነው እንጂ መች አድሎኝ
ገና በሩቁ ሄዷል ገሎኝ
ቀድሞ እየጣለ ስንቱን ገላ
ተራምዶኝ ሄደ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ…….ጉዴ
ጉዴ ፈላ…….ጉዴ
ጉዴ ፈላ…….ጉድ ጉድ ጉዴ
ጉዴ ፈላ…….ጉዴ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ
ጉዴ ፈላ ጉዴ ፈላ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists