ከልቤ እምነቴን ጥላ
በሃሳብ ከኔ እርቃ
የነፍሴን እውነቴን ሽጣ
ከመንፈሴ ላይ ሰርቃ
ሲደለል ሲሸጥ ሲለወጥ
ሲሰረቅ ልቤ ተገርሞ
በድብቅ ፍቅር በስርቆት
በክደት በሌባ ታሞ
እምነቴ ተሸጠ
ፍቅሬ ተለወጠ
ሌባ ነች ሌባ
ስርቆት አመሏ
ሌባ ነች ሌባ
ስርቆት አመሏ
የልቤን ህመም ለፍቅር
ለመውደድ ትቼ ብረሳ
ሞኝነት ሆኖ መፋቀር
ዕውነት ተካደ ተረሳ
መዋደድ ከነፍሷ ጠፍቶ
በሁለት ቢላ ስትበላ
ለሰው መኖርን ሳታውቀው
ሳይገባት የልብ ሥራ
እምነቴ ተሸጠ
ፍቅሬ ተለወጠ
ሌባ ነች ሌባ
ስርቆት አመሏ
ሌባ ነች ሌባ
ስርቆት አመሏ
እምነቴ ተሸጠ
ፍቅሬ ተለወጠ
አካሏ ከኔ ልቧ ከሌላ
ባንድ ገበታ እንዴት እንብላ
ካሌባ ልቧ እምነት ጠፋና
ጨዋታ ሆነ ፍቅር ቀረና
ሌባ ነች ሌባ
ስርቆት አመሏ
ሌባ ነች ሌባ
ስርቆት አመሏ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist