Kishore Kumar Hits

Haleluya Tekletsadik - Algebagnm lyrics

Artist: Haleluya Tekletsadik

album: Tewedaj, Vol. 1


የተከለከለዉ የቤትህ ጎዳና
የቤትህ ጎዳና
ምን ይሆን ልብህን ያረገው ደንዳና
ያረገው ደንዳና
ሚስጥሩ አልገባኝም የእልፍኝህ መዘጋት
የእልፍኝህ መዘጋት
ሰው ጥሩ አይደለም ወይ የሆድን ለማውጋት
የሆድን ለማውጋት
የለም የለም የለም አትሳሳት
አያዋጣም የነበረን መርሳት
ይቅር ይቅር ይሄ ነገር
ያስወቅስሀል ባገር
የምትሰራው እኔ አላማረኝም
ሰው እንደ እቃ ተጥሎ አይገኝም
ገፍተህ ኋላ ላትመልሰው
አሁን ተጨነቅ ለሰው
ደጋጎቹ ያቆዩትን
የሰው ፍቅር ተው አትበትን
ወግ ልማዱን ሳታፈርሰው
እንደጥንቱ እደር ከሰው
የተከለከለዉ የቤትህ ጎዳና
የቤትህ ጎዳና
ምን ይሆን ልብህን ያረገው ደንዳና
ያረገው ደንዳና
ሚስጥሩ አልገባኝም የእልፍኝህ መዘጋት
የእልፍኝህ መዘጋት
ሰው ጥሩ አይደለም ወይ የሆድን ለማውጋት
የሆድን ለማውጋት
አሁን ያየ ኧረ ምን ይልሀል
እንዲህ ስትሆን ሰው ይታዘብሀል
ይቅር ይቅር ይሄ ነገር
ይፈርድብሀሀል ሀገር
ያለፈውን ፍቅር አትዘንጋ
አታቅለው የወዳጅን ዋጋ
ገፍተህ ኋላ ላትመልሰው
አሁን ተጨነቅ ለሰው
ሰው ተጠልቶ ምን ሊወደድ
ሁሉም ገብቶ ይበል ጎርደድ
እንደድሮው ቀርበህ ሰው
የታጣዉን መልሰው
ሸብ ረብ ቢል ደጅህ ኦ ሆ ሆ
ጌጥህ ነው ወዳጅህ ኦ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
ሸብ ረብ ሲል ይታይ ኦ ሆ ሆ
የፍቅርህ ተከታይ ኦ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
ሸብ ረብ ሸብ ረብ
ያልከው ከእልፍኝ ሁሉም ይውጣ
አዲስ አመል ከየት መጣ
ደጉን ጥላ አትገንድሰው
ያለፈዉን እስቲ አስታውሰው
ፀቡን ለቀቅ አርገውና
ያዘዉ ፍቅርን አጥብቅና
የነበረው መፍቀር
በአንተ ጊዜ እንዳይቀር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists