Kishore Kumar Hits

Haleluya Tekletsadik - Alem Shegga lyrics

Artist: Haleluya Tekletsadik

album: Tewedaj, Vol. 1


አለም አለም ሸጋ (ሸጋ)
ለኔ አንተ አለህ ዋጋ
አለም አለም ሸጋ (ሸጋ)
ድረስ አንተ ለግላጋ
ናልኝ የኔ ሎጋ

(ድማምዬ) እንደምነሽ በለኝ
(ድማምዬ) አንስተህ ኮፍያ
(ድማምዬ) ይሄ ነው ዋጋዬ
(ድማምዬ) የፍቅሬ ክፍያ
(ድማምዬ) የመውደዴን ደሞዝ
(ድማምዬ) ካገኘሁን ክብሬን
(ድማምዬ) እኔ አይሰማኝም
(ድማምዬ) ባላገኝም ብሬን
ንብረት ገንዘብ ከጄም ባጣ
አለኝ መውደድ ሺ ሚያመጣ
ውድ ፍቅር ልስጥህ እንካ
ሀብትነቱ የሚያስመካ
በዕንቁ ማይተካ

አለም አለም ሸጋ (ሸጋ)
ለኔ አንተ አለህ ዋጋ
አለም አለም ሸጋ (ሸጋ)
ድረስ አንተ ለግላጋ
ናልኝ የኔ ሎጋ

(ድማምዬ) ሁሌ ምደሰተው
(ድማምዬ) ትልቅ ነሽ ስባል
(ድማምዬ) ልክ እንደአውዳመቱ
(ድማምዬ) ስከበር በባል
(ድማምዬ) አንተ ጎኔ ሆነህ
(ድማምዬ) ቡናዬን ሳፈላ
(ድማምዬ) እመቤቴ ካልከኝ
(ድማምዬ) አያሻኝ የሌላ
ጌታዬ ነህ አንተም ለኔ
ትሞላለህ ሁሌም ላይኔ
ደረትህም መስሎ ጋሻ
ግርማ ሰቶህ በትከሻህ
ሆንክለኝ ማስረሻ

ጀግንነትህ እያስመካኝ
ያንተ ሆኜ ማን ሊነካኝ
የጎንህን ሰው ፈልገህ
የኔን ኩራት አሳድገህ
ያዝከኝ ያዝከኝ ያዝከኝ ኧረ ያዝከኝ
ከፍ አድርገህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists