Kishore Kumar Hits

Haleluya Tekletsadik - Tewedaj lyrics

Artist: Haleluya Tekletsadik

album: Tewedaj, Vol. 1


የማነህ ቆንጆ ቆንጆ ቆንጆ
ተወዳጅ ኩሩ ኩሩ ኩሩ
ውይ ፍቅር ውይ ፍቅር
ውይ መውደድ ውይ መውደድ
ይሉኝታ አሳጣኝ በሩቅ መላመድ

ደስ ትላለች እኔን ደሞ እንዳልከኝ
በወሬ ወሬ ነው የሰማሁኝ
ለኩሰኸኝ ከዛ ዝምታ
ምነው ፍቅር በዳርዳርታ
የአይን ጨዋታ ፍቅር አኩኩሉ
ሳይህ ስታየኝ በሩቅ መዋሉ
ልዩ ዓለም ነው ፍርሃት ደስታ
ደፍረህ ድንገት እስክትመጣ
በል እስኪ አናግረኝ
በሩቅ አትየኝ (አው)
ካፍህ ልስማው ያንተን ቃል
እንጂ አይቻል
ተወዳጁ ወዳጄ
ልይህ ደጄ(አው)
ደስ ትላለች ካልክማ
የኔን ስማ
የማነህ ቆንጆ ቆንጆ ቆንጆ

ተወዳጅ ኩሩ ኩሩ ኩሩ
ውይ ፍቅር ውይ ፍቅር
ውይ መውደድ ውይ መውደድ
ይሉኝታ አሳጣኝ በሩቅ መላመድ

ደስ ብሎኛል ደስ ስላልኩህ
ፀሀይ ሞቆታል ባይኔ ስወድህ
ታዲያ በሩቅ ብቻ መሳሳብ
ጠፍቶ ነው ወዶ ሸጋ ሰበቡ
ጠጋ ልበልህ አንተም ጠጋ በላ
ኩራት ቀንሰህ ና የኔ ሸበላ
ደጄ መተህ ሳታንኳኳ
እንዴት ልበል ልቤን እንካ
በል እስኪ አናግረኝ
በሩቅ አትየኝ (አው)
ካፍህ ልስማው ያንተን ቃል
እንጂ አይቻል
ተወዳጁ ወዳጄ
ልይህ ደጄ(አው)
ደስ ትላለች ካልክማ
የኔን ስማ

በል እስኪ አናግረኝ
በሩቅ አትየኝ (አው)
ካፍህ ልስማው ያንተን ቃል
እንጂ ላይቻል
ተወዳጁ ወዳጄ
ልይህ ደጄ(አው)
ደስ ትላለች ካልክማ
የኔን ስማ
በል እስኪ አናግረኝ
በሩቅ አትየኝ
ካፍህ ልስማው ያንተን ቃል
እንጂ አይቻል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists