Kishore Kumar Hits

Haleluya Tekletsadik - Asheweyna lyrics

Artist: Haleluya Tekletsadik

album: Tewedaj, Vol. 1


በዚህ ዓለም አንተን ነው በልኬ
መርቆ የሰጠኝ አምላኬ
ታድራለች ነብሴ አንተን ሰስታ
ልዩ ነው የማገኘው ደስታ
የኔ ነህ የአዳም ዘር ድርሻዬ
የምልህ የመጨረሻዬ
እያለህ ሄጄ ሌላም አልቃኝ
አምናለሁ ለኔ እንደምትበቃኝ

ሰማዩን ሲያደምቁት
ክዋክብቱ ፈሰው
ውበትህ ተዘራ የማይታፈሰው
ይሄ ያንተ ማማር
ሲመሽ አለው ነገር
የልቤን ፍሰሀ አይ አዬዬ
በምን ቃል ልናገር እእእ
በምን ቃል ልናገር
አሸወይና ወይና ወይንዬ
አ እሻዋለሁ ስደሰት ውየ

የኔዓለም ጀምሪቷ ጠልቃ
የኔዓለም ሲለኮስ ኩራዙ
የኔዓለም ሲጨልም ያበራል
የኔዓለም የአካላትህ ወዙ
የኔዓለም እራትም ተበልቶ
የኔዓለም ቡና እሰከሚያከትም
የኔዓለም እኔ ከአፍህ ሌላ
የኔዓለም አልመለከትም

መደቡ ዳር ሆነን
እሳት እየሞቅን
በደስታ ተንሳፈን
ቦታ እየለቀቅን
ለሩቅ ሰዐት እድሜ
ስንወጣ ከጠፈር
ከዓለም እንጠፋለን አይ አሃሃሃ
ተጎራርሰን ከንፈር እምምም
ተጎራርሰን ከንፈር
አሸወይና ወይና ወይንዬ
ኣኣ እሻዋለሁ ስደሰት ውየ

ላይኖቼ(ላይኖቼ)
ለልቤ (ለልቤ)
አንተ ነህ ርሀቤ(ናና ናና)
በፍቅሬ (በፍቅሬ)
አልጠግብህ(አልጠግብህ)
ባስብህ ባስብህ (ናና ናና)
የምትኖር (የምትኖር)
ታምነህ (ታምነህ)
አሸወይና ነህ (ናና ናና)
ይሟላ (ይሟላ)
ደስታዬ (ደስታዬ)
ካለህ ዘንካታዬ (ናና ናና)
(የምትኖር)
(ታምነህ)
(ናና ናና)
(ይሟላ)
(ደስታዬ)
(ናና ናና)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists