Kishore Kumar Hits

Hewan Gebrewold - Kochegn lyrics

Artist: Hewan Gebrewold

album: Kochegn


እምቢ እንዳልኩህ አላውቅም በጭራሽ
ያስተዋልኩት ሰው ሲለኝ ነው ኮራሽ
ለኔ ባይልህ ስትውል ባይኔ
መች ቀረልኝ መብከንከኔ
ስትቀርበኝ ሸሽቼህ አፍሬ
ስትርቀኝ ልመጣ አፍቅሬ
መች ገባኝ ዞሬ እንደምመለስ
ማለዳ ማለዳ ማለዳ ነው አሉ
መውደድና ፍቅር ልብ የሚባባሉ
ማለዳ ማለዳ ማለዳ መጥቼ
ልመለስ ብቆጭም ዐይንህን አይቼ
ለማን ለማን ለማን
ለማን ሊልህ ነው
ለማን ሊልህ ነው
ፍቅር አንተን ሲተው
እኔን ያለኝ አልተው
ወይ አኩራርቶኝ መፈቀሬ
ልዋልልህ ተግደርድሬ
አንዴ ከእጄ አምልጠሃል
ሸጋ መውደድ ወጥነሃል
ኧረ አንዳንዴ ኧረ አንዳንዴ
ሰው በመላ ነው በዘዴ
የሚያዘው ሲሉኝ ያኔ
መች ታወቀኝ ይሄ ለኔ
ገባኝ ብል ነገሩ ካለፈ
ፍቅርህ ግን ለኔ መች ተረፈ
ነገዬን ሳስብ ከበፊቱ
ገደለኝ ፀፀቱ ቁጭቱ
ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም
ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም
ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም
ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም
ማለዳ ማለዳ ማለዳ ነው አሉ
መውደድና ፍቅር ልብ የሚባባሉ
ማለዳ ማለዳ ማለዳ መጥቼ
ልመለስ ብቆጭም አይንህን አይቼ
በማን በማን በማን
በማን ሊክሰኝ
በማን ሊክሰኝ
ይሆን ሆድ ያስባሰኝ
አንሶ የሚያስነክሰኝ
ይብላኝ እንጂ ለኔው ገላ
አሻፈረኝ ላለኝ ሌላ
ይሁን ብልስ እሺ በቃ
የት ይገኛል የልብ አውቃ
ጥሩ አንዳንዴ ጥሩ አንዳንዴ
ሰው በመላ ሰው በዘዴ
ባላልኩበት ዘመን ያኔ
ነበር ለካስ ልብህ የኔ
ገባኝ ብል ነገሩ ካለፈ
ፍቅርህ ግን ለኔ መች ተረፈ
ነገዬን ሳስብ ከበፊቱ
ገደለኝ ፀፀቱ ቁጭቱ
ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም
ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም
ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም
ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም
ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም
ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም
ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም
ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም
ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም
ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም
ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም
ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists