Kishore Kumar Hits

Hewan Gebrewold - Tfelegaleh lyrics

Artist: Hewan Gebrewold

album: Hewan


አንተስ ለጉድ ትፈለጋለህ
አንተስ ለጉድ ትፈለጋለህ
አንተማ ትፈለጋለህ
ትፈለጋለህ
ፈለኩህ በጣም
እንደ ማር ከጣም
አንተስ ለጉድ ትፈለጋለህ
አንተስ ለጉድ ትፈለጋለህ
አንተማ ትፈለጋለህ
ትፈለጋለህ
ፈለኩህ በጣም
እንደ ማር ከጣም

ማነው ጉዳይ ገዳይ ማን ይሁን አማላጅ
አግባብቶ ሚያረገን እኔና አንተን ወዳጅ
ትንሽ አስጀምሮ ቢያሳየኝ መንገዱን
እኔ አውቅበት ነበር ጨዋታ አካሄዱን
ፈተንከኝ በጣም እድል ፍለጋ

መንገድ ባገኘሁ ካንተ ሚያስጠጋ

ካልቸገረ ጥላ ካልጠፋ ዳስ ሰፈር
ምነው አስጠለልኩት አይኔን ካንተ ከንፈር
ያለ መስተፋቅር
ያለ መስተፋቅር ያለ መድሀኒት
እንዲህ ሰው አፍዝዞ አለ ወይ መቅረት
ካልቸገረ ጥላ ካልጠፋ ዳስ ሰፈር
ምነው አስጠለልኩት አይኔን ካንተ ከንፈር
ያለ መስተፋቅር
ያለ መስተፋቅር ያለ መድሀኒት
እንዲህ ሰው አፍዝዞ አለ ወይ መቅረት

አንተስ ለጉድ ትፈለጋለህ
አንተስ ለጉድ ትፈለጋለህ
አንተማ ትፈለጋለህ
ትፈለጋለህ
ፈለኩህ በጣም
እንደ ማር ከጣም

ስፍስፍ እያረገ አይንህ እያጓጓ
ልቤን ካደረገው በሩን እንዳይዘጋ
ፈላጊህ ነኝ እና ያውም ለቁምነገር
እንግዲህ ላንኳኳ ሰርክ የልብህን በር
ፈተንከኝ በጣም እድል ፍለጋ

መንገድ ባገኘሁ ካንተ ሚያስጠጋ

ጉድ ነው ጉድ ጉድ ጉድ
የትም ይሁን ወራጅ ልቤ ወንዛ ወንዙ
አንተን ተከትሎ ከሆነ መፍሰሱ
የፈጀውን ቢፈጅ
የፈጀውን ቢፈጅ ላግባህ እንጂ ከእጄ
አንተን ሲያምርሽ ይቅር ማን ሊለኝ ወድጄ
የትም ይሁን ወራጅ ልቤ ወንዛ ወንዙ
አንተን ተከትሎ ከሆነ መፍዘዙ
የፈጀውን ቢፈጅ
የፈጀውን ቢፈጅ ላግባህ እንጂ ከእጄ
አንተን ሲያምርሽ ይቅር ማን ሊለኝ ወድጄ
ካልቸገረ ጥላ ካልጠፋ ዳስ ሰፈር
ጉድ ጉድ ነው
አስጠለልኩት አይኔን ካንተ ከንፈር
ያለ መስተፋቅር
ያለ መስተፋቅር ያለ መድሀኒት
እንዲህ ሰው አፍዝዞ አለ ወይ መቅረት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists