Hewan Gebrewold - Alem lyrics
Artist:
Hewan Gebrewold
album: Hewan
የተክልኩት ወይን አምሮልኝ ዘለላው
ቀን እየጠበኩኝ አውርጄ ልበላው
ወፎች ሲሠፍሩበት እያየሁኝ ባይኔ
ወንጭፍ ስላጣዉኝ እላለሁ ወይኔ
ይች አለም ስታጠፋው ሀቁን ሰዉራ
ስለሷ ምን ላውራ
ለለፋ ብቻ አትሞላ ለደከመባት
ሰምም ወርቅ አለባት
ለጊዜው እንካ ብትል ሰውን ለይታ
ልትቀማው ቆይታ
እንዲ ነች ሲሏት እንዲያ ማን ደረሰባት
ዓለም ውል የለባት
♪
እህ አንዱን ከፊት
እህ አንዱን ኋላ
እህ አንዴ ጭንቀት
እህ ደሞ መላ
ይች አለም ስታጠፋው ሀቁን ሰዉራ
ስለሷ ምን ላውራ
ለለፋ ብቻ አትሞላ ለደከመባት
ሰምም ወርቅ አለባት
ለጊዜው እንካ ብትል ሰውን ለይታ
ልትቀማው ቆይታ
እንዲ ነች ሲላት እንዲያ ማን ደረሰባት
ዓለም ውል የለባት
♪
አሄሄ-
አሄሄ-
♪
አሄሄ-
♪
አሄሄ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist