Hewan Gebrewold - Mn Ytqmehal lyrics
Artist:
Hewan Gebrewold
album: Hewan
እራሴን ሆኜ መኖር
ታውቃለህ ልምዴ ነበር
ታዘብኩት ይሄን ምድር
ጣፋጩም ጊዜ ሲመር
ሸርተት አለ ጎኔ መከዳው
ጉዳይ መምሰል እንዳልተጎዳው
ሸፋፈንኩት እየተቀጣሁ
አንተን ላተርፍ ብዬ እኔን አጣሁ
♪
የሆንኩልህ የምንጭ ውሃ
የቆጠርከኝ ከበርሀ
ተረዳሁት ሞኝነቴን
ድንገት ሳጣው ካንተ እምነቴን
ህመምስ ይጎዳል ምነኛ
ቢችሉት እንደ ደስተኛ
ሀዘኔን ደብቄው ሰው መሀል
ማረሬ ቆይ ምን ይጠቅምሀል
ምን ይጠቅምሀል ምን ይጠቅምሀል
ማደር ከንባዬ ካይኖቼ መሀል
ምን ይጠቅምሀል ምን ይጠቅምሀል
ማደር ከንባዬ ካይኖቼ መሀል
♪
እራሴን ሆኜ መኖር
ታውቃለህ ልምዴ ነበር
ታዘብኩት ይሄን ምድር
ጣፋጩም ጊዜ ሲመር
ሸርተት አለ ጎኔ መከዳው
ጉዳይ መምሰል እንዳልተጎዳው
ሸፋፈንኩት እየተቀጣሁ
አንተን ላተርፍ ብዬ እኔን አጣሁ
♪
ነው ወይ ፍቅር የጅል ተረት
ወድያ አልሞ ወዲህ መቅረት
ተገን ያሉት ላይሆን ደስታ
ልቤን ጣልኩት ካጉል ቦታ
እንግዲ ፍርዴ ነው መብሰልሰል
ነገሩ ተከድኖ ስል ይብሰል
ባወራው አንተን ይጠሉሀል
ግን እኔ ተጎዳሁ በመሀል
ምን ይጠቅምሀል ምን ይጠቅምሀል
ማደር ከንባዬ ካይኖቼ መሀል
ምን ይጠቅምሀል ምን ይጠቅምሀል
ማደር ከንባዬ ካይኖቼ መሀል
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist