ወዲያም ወዲህ ማዶ
ሳለ ሰው ተዋዶ
እንደኔ እንደኔ እንደኔ እንደኔ
የለም በማፍቀር ሀጥያት ኩነኔ (አሄ)
እንደኔ እንደኔ አዎ እንደራሴ
በመውደድ ሀጥያት አትገባም ነፍሴ (አሄ)
♪
አሀ ሀይ
ግርማው የንጉስ ሞገስ ተላብሶ
ፍቅር የሚሰጥ ክንግ አንተርሶ
ተገኝቷል ወዳጅ ቤቴ በላይ
አምባው ላይ አምባው ላይ
ቁመተ ሎጋ ጠይም ጎፈሬ
ሺ ገዳይ ገዳይ ሞልቶ ሰፈሬ
ተመላለስኩኝ ስንቴ ደጁ ላይ
አይኑን ላይ አይኑን ላይ
መልኩ ከፀባይ ነፍስ የሚያጠራ
ሰማኹኝ ቃል ልቤን ሲጠራ
እያለ ሲከንፍ ሰው በፍቅር
እኔስ ለምን ልቅር
ምን ይሉኝ ብዬ ገና ለገና
አይሆንማ ጎጆም አይቀና
ሆነም አልሆነ አንድ ሞት ላይቀር
ግፍ የለውም ማፍቀር
አሀ ሀይ (አይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (ወይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (አይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (ወይ ፍቅር)
♪
ወዲያም ወዲህ ማዶ
ሳለ ሰው ተዋዶ
እንደኔ እንደኔ እንደኔ እንደኔ
የለም በማፍቀር ሀጥያት ኩነኔ (አሄ)
እንደኔ እንደኔ አዎ እንደራሴ
በመውደድ ሀጥያት አትገባም ነፍሴ (አሄ)
አሀ ሀይ
ላብ ባጠመቀው የክቱ ልብስ
በጁ ቢነካኝ ልትወጣ ነፍሴ
ተግኝቷል ሸጋ ቤቴ በላይ
አማላይ አማላይ
በጉራማይሌው ሳቅ ለፈተና
ሳልዘገጃጅ ተያስኩኝና
አጣሁ አማላጅ የፍቅር ሸንጋይ
ገላጋይ ገላጋይ
መልኩ ከፀባይ ነፍስ የሚያጠራ
ሰማኹኝ ቃል ልቤን ሲጠራ
እያለ ሲከንፍ ሰው በፍቅር
እኔስ ለምን ልቅር
ምን ይሉኝ ብዬ ገና ለገና
አይሆንማ ጎጆም አይቀና
ሆነም አልሆነ አንድ ሞት ላይቀር
ግፍ የለውም ማፍቀር
አሀ ሀይ (አይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (ወይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (አይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (ወይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (አይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (ወይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (አይ ፍቅር)
አሀ ሀይ (ወይ ፍቅር)
አይ ፍቅር
ወይ ፍቅር
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist