Kishore Kumar Hits

Veronica Adane - Kurfya lyrics

Artist: Veronica Adane

album: Kurfya


እያዋለ ስሜን (አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ከሰው አፍ ሊያበዛ (አይ ኩርፊያ አይ አመል)
አውቆታል መሰለኝ ልቤን እንደገዛው
ይናፍቀኝ ጀመር ኩርፍያው ከነው ለዛው
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ተቆራኝቷልና ከአካል ከመንፈሴ
ላሽሞንሙነው የእኔን መውደድ እንደራሴ
ልቤ ሰፍ አታርገኝ ይመጣል በጊዜ
እያለም አልቻልኩት የፍቅሩን አባዜ
በቀላል በመልካም በቀላል
ካሰብኩት ሲመሻሽ ብቅ ይላል
እያልኩኝ እራሴው
ሳወራ ለራሴው
የፍቅር ፀጋህን
ወደድኩት ኩርፊያህን
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይናፈቅ ጀመር እያደር
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይወደድ ጀመር ይፈቀር
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ያመኑት ሰው እንከን ባይወጣም በጥድፊያ
ካዳም ልጅ ፀባይ ላይ መች ይታጣል ኩርፊያ
ከህመሙም በላይ ለሀሳብ ከመስጠቱ
ፍቅር ነው የታየኝ በልጦ ከቅብጠቱ
በቀላል በመልካም በቀላል
ካሰብኩት ሲመሻሽ ብቅ ይላል
እያልኩኝ ጠርጥሬው
ቀስ በቀስ ጀምሬው
አረፍኩት ለምጄ
ኩርፊያህን ወድጄ
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይናፈቅ ጀመር እያደር
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይወደድ ጀመር ይፈቀር
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
ፍቅር ሲያሰቃየው (አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ካመሉ ቀን በቀን
ከኩርፊያው የማያውቅ (አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይናፈቅ ጀመር እያደር
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይወደድ ጀመር ይፈቀር
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)
ይናፈቅ ጀመር ይናፍቅ ጀመር (አይ ኩርፊያ አይ አመል)
(አይ ኩርፊያ አይ አመል)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists