Illasha Fekadu - Tikitu Yibekal lyrics
Artist:
Illasha Fekadu
album: Endegena
በአመፅ ከተገኘ ግዝፈት የፍቅር ትንሹ ይበልጣል
ከኃጥያተኛው መትረፍረፍ የፃድቁ እጦት ይበቃል
ሞት ካጠላበት ከትልቁ ዋርካ የህይወት ችግኝ ብልጫ አለው
ከጨለማ ከማያልቅ አምሮት ብርሀን ብቻውን አርኪ ነው
የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል
ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል
የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል
ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል
ለራስ ለስጋ ከሚሸጥ ነፃነት የፍቅር ባርነት ይበጃል
በግፍ በእብሪት ከዳበረን እምነት የቱትራስ መካድ ይሻላል
ትርጉም ለሌለው ለውሸት ከመኖር ለእውነት መሞት ክብር ነው
መጽሐፍ እንደሚል የእግዜር ሞኝነት ከሰዎች ጥበብ ጠቢብ ነው
ለሞት ትርፍ ህይወት ብከፈል ምን ትርጉም አለው
ስጋችን በቃኝ አያውቅም ጥበብ በመደራት ነው
ጣፋጩን መብል ፍለጋ ኑሮን ከማምረር
ዋናውን በልብ አንግሶ ህይወት ማሳመር
የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል
ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል
የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል
ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል
ንጹን መልካሙን መውደድ መውደድ
ቅዱሱን ፍፁሙን መፈለግ
ከአለም ከንቱ ክምችት ክምችት
ጥቂቱን በቂውን መሻት
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist