Kishore Kumar Hits

Illasha Fekadu - Beretahu lyrics

Artist: Illasha Fekadu

album: Endegena


ከመንታዬ ስነሳ
ማለዳ ከአልጋዬ ስወርድ
ትላንት እንቅልፍ ከነሳኝ
ከሀሳብ ጓዋዜ ጋር ልነጉድ
የእየለቱ ምግቤ
ምህረትህን አቃልዬ
ደግሞ ነጋብኝ አልኩኝ
አንተ ላይ ፊቴን አጥቁሬ
ያልታዘዝልኝ ሸክም
በጣም ስለተጫነኝ
የሚያዥ የሌለው ክብደት
እንዳጎበጠኝ አዋለኝ
ሸክሜ እጅግ አስጎንብሶኝ
ማዬት ስለተሳነኝ
ካገኘሁት ስላተም
ስነጫነጭ አዋለኝ
እቤቴ በጊዜ ገባሁኝ
አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩኝ
በፀጋ ብርታት ነቃሁኝ
ቃልህን አነሳው
አቅሜን ተረታሁኝ
በእኔ ጣለው ስትል ሰማሁኝ
በድንገት እርፍ አልኩኝ
የከበደኝን ሁሉ ጣልኩኝ
ኦኦኦኦ በረታሁኝ
በእጅህ በመንፈስ በረታሁኝ
ከእንቅልፌ ስነቃ
ስጀምረው ቀኔን አዲሱን
ትላንት በእርዳታ የተወኝ
ደግም ተነሳ ሊያደረግ ልማዱን
የእየ እለቱ ምግቤን
ፍቅርህን አጣጥሜ
እሳይ ነጋልኝ አልኩኝ
ጭንቄቴን በአንተ ጥዬ
ትላንት ያጎበጠኝን
እረፍት ያሳጣኝን ሁሉ
ከአእምሮዬ ወሰድከው
ሰላም ሞለኅኝ በምትኩ
አንተ የሰጠኅኝ ሰላም
አእምሮዬን ስላለፈ
ፈገግታዬ ደመቀ
ደስታዬ ለሁሉ ታወቀ
ደስታዬ የገረማቸው
ጥያቄ ፍጥሮባቸው
አልዋጥ አላቸው ለውጤ
ሰላሜ ታዬ ከውስጤ
ሚስጥሬን ገለጥኩ እንዲሁ
ሰላም ለተጨነቀው
ምንጭ ከእላይ ነው በነፃ
ሸክምን ከትከሻ የሚያነሳ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists