ለብቻው መራመድ እንደማይችል ሕጻን ልጅ ነኝ
ከመዳህ አንስተህኝ መሄድን አስተምረኝ
ሙሉ ሰው ወደመሆን ወደ ሙላትህም ልድረስ
ዕለት በዕለት እንዳድግ ልቤን አፅና አድስ
ማዳንን ያውቃል አድኖም ይጠብቃል
በሕይወት ጎዳና ላይ አለሁልህ በርታ ይላል
የልጆቹን ፀጉር እንኳ በቁጥር ይዞታል
ብላቴንነቴን አውቆ ጌታዬ ለልጁ ይዋጋል
መቆሜም መኖሬም ባንተው ባለኝ እምነቴ ነው
የሱስ ሆይ ካንተ ጋር ባልሆን መውደቅያዬ አይጣል ነው
በፊቴ ያለውን ሩጫ ስሮጥ ድምጽህ ያጽናናኝ
ነገን በእጅህ የያዝክ እጄን ደግሞ ያዘኝ
የምትወደኝ አምላክ ድልንም የሰጠኸኝ
ውጊያው ያንተ ፋንታ ነው እኔ አመስጋኝ ነኝ
ደካማው ጎኔን ጠግን መርምረኝ አክመኝ
ፍጥረትን ሁሉ የያዝክ እጄን ይዘህ ምራኝ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist