Kishore Kumar Hits

Eyasu Teklemariam - Ayenegerem (Unspeakable Gift) lyrics

Artist: Eyasu Teklemariam

album: From Every Nation


ቋንቋ ገደበኝ ብዬ ዝም አልልም
ምስጋናዬን እጨምራለሁ ባይመጥንህም
ብቻውን የሰዎች ልሳን ገልጾ አይችለው
መላዕክት ቃልን አውሱኝ ውዴን ላድንቀው
የፍቅር አምላክ የምህረት ጌታ
ባንተ ጸጋ ክለላ ነው ያለፍነው ዘመኑን
አይነገርም ስጦታህ
አይቆጠርም ቸርነትህ
ኢየሱሴ መልካም ነህ
መድኃኒቴ መልካም ነህ
ጠላትና ቂመኛውን ትበቀል ዘንድ
በለሊት ዝማሬን በአፌ ጨመርክ
በገና ሆይ በል አንተም ተነስ በማለዳ
አዕዋፍ ሳይቀድሙኝ ላምልክ ውዴን በዜማ
የፍቅር አምላክ የምህረት ጌታ
ባንተ ጸጋ ክለላ ነው ያለፍነው ዘመኑን
አይነገርም ስጦታህ
አይቆጠርም ቸርነትህ
ኢየሱሴ መልካም ነህ
መድኃኒቴ መልካም ነህ
መልካም ነህ በደስታ
መልካም ነህ ችግር ቢመጣ
መልካም ነህ በጥበቃህ
ልዑል ሆይ ስለ ሁሉ ተባረክ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists