Kishore Kumar Hits

Eyasu Teklemariam - Medhaneten (Kante) lyrics

Artist: Eyasu Teklemariam

album: Zemenat Aylewetuhem


መድኃኒቴን ፡ አየዋለሁ ፡ ዓይኖቼ ፡ ተከፍተዋል
በደሙና ፡ በስሙ ፡ ስላነጻን
ፍፁም ፡ ህይወት ፡ አሁን ፡ አለኝ ፡ በሞቱ ፡ ፈወሰኝ
አሮጌው ፡ ልማድ ፡ ከሕይወቴ ፡ ጠፍቷል
አዝ :- አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ሥሙንም ፡ ልወድስ
ስላፈቀረኝ ፡ በመስቀል ፡ ተሰቅሎ (ሃሌሉያ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱሴን ፡ ልወድስ
ለዓለም ፡ ህዝቦች ፡ የፍቅሩን ፡ ወንጌል ፡ ልግለጽ (፪x)
ትኩስ ፡ ቀዝቃዛ ፡ ለብ ፡ ያለ ፡ ህይወት ፡ አትመኑ
የጌታ ፡ አገልጋይ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ነው
በመንፈስ ፡ እሳት ፡ ግላቹህ ፡ እርሱን ፡ አገልግሉ
የድሉን ፡ አክሊል ፡ እንድትቀበሉ
አዝ :- ፡ አምላኬን ፡ ላመስግን ፡ ሥሙንም ፡ ልወድስ
ስላፈቀረኝ ፡ በመስቀል ፡ ተሰቅሎ (ሃሌሉያ)
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱሴን ፡ ልወድስ
ለዓለም ፡ ህዝቦች ፡ የፍቅሩን ፡ ወንጌል ፡ ልግለጽ (፪x)
ነፍሴ ፡ አርፋለች ፡ በዙፋንህ ፡ ሥር
በጥላህ ፡ እታመናለሁ
መፍትሄ ፡ የሌለው ፡ ምንም ፡ ችግር
እንደማያገኘኝ ፡ አውቃለሁ
ከአንተ ፡ የተሻለ ፡ ጓደኛ ፡ የለኝም
ከአንተ ፡ የቀረበ ፡ ዘመድ ፡ አላገኝም
ከአንተ ፡ የበለጠ ፡ ምንም ፡ አልመኝም
ሆሆሆ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልኝ ፡ ምንም ፡ አይጐለኝም (፫x)
Writer- Mignot Dansa

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists