ዘምን ፡ በዘመን ፡ ሲፈራረቅ
ቀኑም ፡ ለቀኑ ፡ ቦታም ፡ ቢለቅ
በዓመታት ፡ መሃል ፡ በቀናት ፡ ቁጥር
ከፍ ፡ ከፍ ፡ እያልክ ፡ የምትከብር (፪x)
የጊዜ ፡ ኃይል ፡ አይለውጥህም
አንተ ፡ ህያው ፡ ነህ ፡ አትቀየርም
ሚመስልህ ፡ የለም ፡ የሚገዳደርም
ማነው ፡ ኃይልህን ፡ የሚከለክልህ (፪x)
አዝ :- ፡ ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ ዓመታት ፡ አይሽሩህም
ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ
ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
ቢፈራረቁ ፡ ክረምት ፡ ከበጋ
አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ
ጊዜው ፡ ሲገሰግስ ፡ እንደ ፡ ሰረገላ
አንተ ፡ አታረጅም ፡ አትቀርም ፡ ኋላ (፪x)
ሁሉ ፡ ፈጥረሃል ፡ በስልጣንህ
ተከናወነ ፡ በይሁን ፡ ቃልህ
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ስንት ፡ ነዋሪ
አቻ ፡ የለህም ፡ ተወዳዳሪ ፡ ተገዳዳሪ
አዝ :- ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ አመታት ፡ አይሽሩህም
ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ
ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (የሚመስልህ ፡ የለም)
የጥንቱ ፡ ክንድህ ፡ ይሰራል ፡ ዛሬም
ግሩም ፡ ችሎታህ ፡ አልተቀየረም
አንተ ፡ አትሻር ፡ አትለወጥም
ኢየሱስ ፡ ህያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)
በሙሴ ፡ ዘመን ፡ ባህሩን ፡ ከፍለህ
በሐዋርያት ፡ ማዕበሉን ፡ ገሰጽክ
ብዙ ፡ ሰርተሃል ፡ በየዘመናት
እጅግ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ተዓምራት
አዝ :- ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ አመታት ፡ አይሽሩህም
ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ
ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x)
ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ አመታት ፡ አይሽሩህም
ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ
ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፬x)
Writer- Mignot Dansa
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist