Kishore Kumar Hits

Eyasu Teklemariam - Girumu Yesus lyrics

Artist: Eyasu Teklemariam

album: Zemenat Aylewetuhem


እኔ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሳልመጣ
ገና ፡ ኃጢአተኛ ፡ ሳለሁ
ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ ተገለጠ
በፀጋህ ፡ ድኛለሁ
አዝ :- ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ይገርመኛል
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ከጥፋቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ አድኖኛል
(ይገርመኛል ፡ ኢየሱስ... ለኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር... ሃሌሉያ)
አንተ ፡ ለነፍሴ ፡ መቸገር ፡ አልነበረብህም
ግን ፡ አምላኬ ፡ በኔ ፡ ፍቅር
ነፍሴን ፡ ችላ ፡ አላልካትም
አዝ :- ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ አፍቅሮኛል
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ አለኝታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ለውጦኛል ፡
(ነፍሴ ፡ ወደደችህ... ግሩሙ ፡ ኢየሱስ
ነፍሴ ፡ ወደደችህ... ሃሌሉያ (፪x))
የሰማይን ፡ ዕርዝመት ፡ ያወቅህ ፡ የመረመርከው
የምድርን ፡ ሚስጥር ፡ የያዝክ
እኔን ፡ የፈጠርከው
አዝ :- ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ቻዩ ፡ ጌታ
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ታግሶኛል
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ብበድልም
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ አንጽቶኛል
(ይገርመኛል ፡ ኢየሱስ... ለኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር... ሃሌሉያ)
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ይገርመኛል
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ከክፋቴ
ግሩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ አድኖኛል
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ አፍቅሮኛል
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
ፈቃዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ለውጦኛል
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ቻዩ ፡ ጌታ
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ታግሶኛል
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ ብበድልም
ታጋሹ ፡ ኢየሱስ ፡ አንጽቶኛል
Writer- Mignot Dansa

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists