Kishore Kumar Hits

Tsedi - Hiywet lyrics

Artist: Tsedi

album: 2:11


ትደርስበታለህ
ውሃ እያለ ከተጠማው
ተስፋ ማየት ካልፈለገው
ሰው በያዘው ከሚቀናው
በተሰጠው ከማይኮራው
ከራሱ ጋር ከተጣላው yeah
እርቃለሁ የተሰጠኝ ብዙ አለኝ
የምሰጠው ብዙ ነው
የህይወቴን ክፍተቶች በተስፋ ነው ምሞላው
አንድ ነገር አውቃለሁ የእኔ ህይወት ትርጉም አለው
ለወደዱኝ ለመኖር ለመቅረት ነው የምጥረው
የኔ ህይወት
የኔ ነው የምኖረው
ምጠብቀው
ህይወት የኔ ነው
የተሰጠኝ ስጦታ ነው

ትደርስበታለህ

ተምሬያለሁ ከሚሰራው
የጊዜን ዋጋ የገባው
የሚታየው መልካም ነገር
የማያገኝ የራሱን ነገር
በችግሮች ማይሸበር
መፍትሔ አለው ለሁሉም ነገር
ኖሮ ሚያሳይ
ማይናገር መርጫለሁ
የተሰጠኝ ብዙ አለኝ የምሰጠው ብዙ ነው
የህይወቴን ክፍተቶች በተስፋ ነው ምሞላው
አንድ ነገር አውቃለሁ የእኔ ህይወት ትርጉም አለው
ለወደዱኝ ለመኖር ለማብረፅ ነው ምጥረው
ህይወት የእኔ ነው
የምኖረው ምጠብቀው
ህይወት የኔ ነው
የተሰጠኝ ስጦታ ነው

አትደውል እኔ ጋር ግዜ የለኝ ለመዶለት
ነው ባለኝ ለመስራት እምቢ መጎለት
እንዲህ ስንል እንዲያ ከህይወት ነው መፎረሽ
እኔ አላማ አለኝ ተው
እኔም አልገኝ በህይወት ከመፎረሽ
አላማ አለኝ ግዜ የለኝ ለመጎለት
እኔ ማለት እንዲህ ነኝ በቃ ተወኝ
አላማ አለኝ ተው
የኔ ህይወት የኔ ነው
የምኖረው ምጠብቀው
ህይወት የኔ ነው
የተሰጠኝ ስጦታ ነው
ትደርስበታለህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists