Tsedi - Halo lyrics
Artist:
Tsedi
album: Sew
እንደ ደመናው የራቀኝ
ግን የኔ መስሎ ሚደልለኝ
ፍቅሩን ከልቤ አስቀምጦ
ፍቅሬም አዲስ ዓለም አይቶ ወጥቶ
እንዳወከኝ ሲሰማኝ
እውነቱን ባውቅም እየካድኩኝ
ብታቀለው የሷን ነገር
ራሴን የወደድኩት ያኔ ነበር
♪
እንደ ጠዋት ጀምበር ቀኔን ስላፈካው
ፍቅርህን ፈለኩት የግሌ ላደርገው
የፍቅርህ ሚዛኑ ለማን እንዳደላ
ቢረፍድም ገብቶኛል የኋላ የኋላ
ስል ሃሎ ሃሎ ሃሎ
ውስጤ ናፍቆ ሊያይህ ጓጉቶ
ስልኩን እንዳነሳሁት ጠራኸኝ በስሟ
ልብ አልኩት
ሃሎ ሃሎ ሃሎ
ልቤ ደሞ ደሞ አስቦ
ብዙ ብዙ አይቶሃል
አመንኩኝ የርሷ ፍቅር ቀድሟል
♪
ልቡ ተካፍሎ እንዳስጨነቀው
እሷ ባታውቅም እኔ አውቃለሁ
አይሆንም ብዬ ስል ልተወው
ሲያወራኝ ደሞ አምነዋለሁ
የኔን መራቅ ባትፈልግም
ያንተ ማድረግ ደግሞ አትችልም
ፍቅርህ ብዙ አስተምሮኝ
ሳልቀየምህ ሄጃለሁኝ
♪
እንደ ጠዋት ጀምበር ቀኔን ስላፈካው
ፍቅርህን ፈለኩት የግሌ ላደርገው
የፍቅርህ ሚዛኑ ለማን እንዳደላ
ቢረፍድም ገብቶኛል የኋላ የኋላ
እሷም ልክ እንደኔ እቅፍ አድርጋህ
አየሁኝ ፎቶ
ያ ሚያምረው ፊትህ
በፍቅር ሲያያት ያማል
አልችልም ከንግዲህ ማሰብ የኔ ነህ ብሎ
ከህልም ዓለሜ ልንቃ ቶሎ
ስል ሃሎ ሃሎ ሃሎ
ውስጤ ናፍቆ ሊያይህ ጓጉቶ
ስልኩን እንዳነሳሁት ጠራኸኝ በስሟ
ልብ አልኩት
ሃሎ ሃሎ ሃሎ (ሃሎ ሃሎ)
ልቤ ደሞ ደሞ አስቦ (ደሞ)
ብዙ ብዙ አይቶሃል
አመንኩኝ የርሷ ፍቅር ቀድሟል
ስል ሃሎ ሃሎ ሃሎ
ውስጤ ናፍቆ ሊያይህ ጓጉቶ
ስልኩን እንዳነሳሁት ጠራኸኝ በስሟ
ሃሎ ሃሎ ሃሎ
ልቤ ደሞ ደሞ አስቦ
ብዙ ብዙ አይቶሃል
አመንኩኝ የርሷ ፍቅር ቀድሟል
ሃሃ-ሃሃ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist